የቤተክርስቲያንና ማህበረሰብን አቅም ማጎልበት ክፍል

ስለ መምሪያው

አጠቃላይ መግለጫ

የቤተ ክርስቲያንና ማኅበረሰብ ማብቃት አገልግሎት በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ዘርፍ ስር መስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም (Sept 1, 2025) የተጀመረ አገልግሎት ነው። አገልግሎቱ አብያተ ክርስቲያናት በእጃቸው ያለውን አምላክ የሰጣቸውን አቅም በመጠቀም በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚ ዘርፍ እራሳቸውንና ማኅበረሰባቸውን እንዲያበቁ ማሰልጠን፣ ማስታጠቅና ማንቀሳቀስ ላይ ያተኩራል። 

 

ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ

  • ራዕይ፦ እያንዳንዱ ግለሰብ በማኅበራዊ ሕይወት የበቃ፣ በኢኮኖሚ የታጠቀ፣ በመንፈሳዊነት የጸና እና እግዚአብሔር የሰጠውን ዓላማ የሚፈጽምበት የነቃች ቤተ ክርስቲያንና ማኅበረሰብ ማየት። 
  • ተልዕኮ፦ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ያካተተ ሁለንተናዊ አቀራረብን በመጠቀም አብያተ ክርስቲያናትንና ማኅበረሰቦችን በማብቃት የሰዎችን ሕይወት መለወጥ። 
  • የአገልግሎቱ ዓላማ፦ ሰዎች በክርስቶስ እንዲያድጉ፣ አምላክ የሰጣቸውን አቅም እንዲያወጡና በወንጌል እውነት አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ እግዚአብሔርን ማክበር። 

ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች

  • የሀገር ውስጥ አቅምን ማሳደግ፦ የአነስተኛ ንግድ፣ የማይክሮ ፋይናንስና የሀገር ውስጥ የፋይናንስ አቅሞችን ማጎልበት። 
  • ማኅበራዊና አካባቢ ጥበቃ፦ በጤና፣ በእርሻና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፎች ተግባራዊ ትምህርቶችንና ድጋፎችን መስጠት። 
  • መሪዎችን ማስታጠቅ፦ የአካባቢ ቤተ ክርስቲያን መሪዎችንና አባላትን ማሰልጠንና ለውጥ አምጪ ማድረግ። 

ዋና ዋና እሴቶች

  • ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ሕይወት 
  • ፍቅርና ርኅራኄ 
  • ታማኝነትና መጋቢነት 
  • ሰዎችን ማብቃትና ማስታጠቅ 
  • የማኅበረሰብ ለውጥ 
  • ጸሎትና በመንፈስ ቅዱስ መደገፍ 
  • አገልጋይ አመራር 

አጋር ድርጅቶች

  • EKHCDCM 
  • ቲርፈንድ ኢትዮጵያ (Tearfund Ethiopia) 
  • ፓርትነርስ ወርልድዋይድ (Partners Worldwide) 

ፎቶዎች

የመምሪያው አመራር

ስም

የመምሪያ ኃላፊ

የመምሪያው የመገናኛ መረጃ

ሞባይል: +251-9 12 34 56 78
ቢሮ: +251-9 12 34 56 78
ፋክስ: +251-9 12 34 56 78
ኢሜይል: @ekhc.et