ታሪካዊ ዳራ
የቤተክርስቲያኒቱ አመሰራረት ታሪክ የሚጀምረዉ በእግዚአብሄር አምላክ ጥሪና በመንፈስ ቅዱስ ምሪት መነሻቸዉን ባህር ማዶ ካደረጉ የኤስ አይ ኤም የወንጌል መልዕክተኞች በእንግድነት ምድር በመንከራተትና መስዋዕትነት በመክፈል ከ1920 ዓ.ም የካቲት ወር ጀምሮ ካመጡት የምስራች ቃል ብስራት ጋር ተያይዞ ህዝቦችንን ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ካሸጋገረው የወንጌል ስርጭት ታሪክ ሂደት ጋር ተያይዞ የቀጠለ ንቅናቄ ውጤት ነዉ፡፡
በእነኘሁ ጥቂት የወንጌል መልዕክተኞች መሣሪያነት የተለኮሰዉ የምስራች ቃል ችቦ ጥቂት በነበሩ የየመንደሩ ወጣቶች አስደናቂ መሰጠትና ሁለንተናቸዉን ለበራላቸዉ የወንጌል አገልግሎት በማዋላቸዉ በአጭር ጊዜ የምስራች ቃሉ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሎ የባዕድ አምልኮ ጨለማን በመግፈፍ በየማሕበረሰቡ አስደናቂ መንፈሳዊና ማሕበራዊ ለዉጦች እየተመዘገቡ በንጽጽር ሲታይ አሁን ላለንበት ከአዕምሮ በላይ ለሆነ እድገትና እምርታ መድረሳችን በእጅጉ ያስደንቃል፤ ያስገርማል፡፡
ከላይ በአጭሩ በተገለጸዉ የአምላካችን አስደናቂ ዕቅድና ክንዉን እንዲሁም በጥቅት ሚስዮናዊያን ፈር ቀዳጅነትና በቀደምት አባቶች ያላሰለስ ተጋድሎና መስዋዕትነት የተነሳ ዛሬ የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን በመላ የሀገራችን ክፍሎችና በአለም አቀፍ መድረኮች ከጠባቂዋና ከመሪዋ የተሰጣትን፣ መንግስቱን በምድር የማስፋፋትና ነፍሳትን ወደ ዘላለም ህይወት የመማረክ ተልዕኮዋን በመፈጸም ላይ ትገኛለች፡፡
ቤተክርሲቲያኒቱ በምድር ላይ የመኖሩዋ ዋና ዓላማ የሆነዉን ነፍሳትን ወደ ድነት ማምጣትና የእግዚአብሔርን መንግስት የማስፋት ሥራዋን ለመፈጸም ከዋና ጽ/ቤት ጀምሮ እስከ አጥቢያዎች ድረስ በተደራጁ መዋቅሮች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አገልጋዮችና ሰራተኞችን አሰማርታ ሁለንተናዊ አገልግሎት ትሰጣለች፡፡
በቤተክርሲቲያኒቱዋ የተለያዩ መዋቅሮች የተሰማሩ አገልጋዮችና ሠራተኞች የአገልግሎት ዘመናቸዉን ፈጽመዉ በጡረታ ሲገለሉ የሚደርስባቸዉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተገዳሮቶች ለመkkምና ለማስወገድ ታስቦ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የማኀበራዊ ዋስትና ኮሚሽን በመጋቢት 22 ቀን 1999 ዓ.ም በሲዳማ ያናሴ አፈራራ በተካሄደዉ 46ኛው ጠቅላላ ጉባዔ የተመሰረተ ሲሆን፣ የቤተክርሲቲያኒቱ አገልጋዮችና ሠራተኞች በጡረታ ዋስትና ደንብ እንዲተዳደሩ በተወሰነው መሰረት የጡረታ መመሪያ ደንቡን ከተመሳሳይ እህት ቤ/ክ እና ከመንግስት ማህበራዊ ዋስትና የጡረታ አዋጅ ተወስዶ በአውዱ መሰረት መሻሻል ያለበት አንቀጾችን በማስገባትና በማሻሻል ብቁነቱ በሕግ ባለሙዎች ተረጋግጦ ከየካቲት 1 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ በዋና ጽ/ቤት በማስተባበሪያ ደረጃ ቢkkምም ቤተክርስቲያናችን ከደረሰችበት የመንፈሳዊና የማህበራዊ የልማት እድገት ሥራዎች አገልግሎት እየሰፋ በመምጣቱ የአገልጋዩ እና የሠራተኛው ቁጥር እየጨመረ ስለመጣ በዋና ጽ/ቤት ዋና ቢሮ በመክፈትና በሁለት ትልልቅ ቀጠናዎች የቅርንጫፍ ቢሮዎችን በመክፈት ቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ጠባቂነት በቦርድና በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በመመራት በቁጥር በርከት ያሉ አባላትን በማኀበራዊ ዋስትና ፈንድ ውስጥ በማካተት ከ100 በላይ የሆኑ አባቶችንና እናቶችን የማህበራዊ ዋስትና አበል ተጠቃሚ በማድረግ እየሠራ ይገኛል ፡፡
አብይ ተግባራት
ራዕይ
በቤተክርሲቲያኒቱ መዋቅር ዉስጥ ያሉ ሁሉም አገልጋዮችና ሠራተኞች በዕድሜም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ከአገልግሎትም ይሁን ከሥራ ስሰናበቱ የዘለቄታ ማኀበራዊ ዋስትና ተጠቃሚ በመሆን ከሚደርስባቸዉ እኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀዉስ ተላቀው ማየት፣
ተልዕኮ
እሴቶች

የመምሪያ ኃላፊ
ሞባይል: +251-9 12 34 56 78
ቢሮ: +251-9 12 34 56 78
ፋክስ: +251-9 12 34 56 78
ኢሜይል: @ekhc.et