የክርስቲያናዊ ጋብቻና የብሔራዊ ጸሎት አገልግሎት

ስለ መምሪያው

የአገልግሎቱ አጠቃላይ ዓላማና መዋቅር፦

 

  • የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የጋብቻ፣ ቤተሰብና ብሔራዊ የተሐድሶ ጸሎት አገልግሎት ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረትን ተክቶ የቤተክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ አእምሮአዊ፣ ስሜታዊና አካላዊ ዕድገት መልክ ለማስያዝ በአዲስ መልክ ከተደራጀ ከ15 ዓመታት በላይ ሆኖታል። 
  • ክፍሉ በሁለት ዋና ዋና ንዑሳን ክፍሎች የተከፈለ ነው፤ እነርሱም ጋብቻና ቤተሰብ እንዲሁም ብሔራዊ የጸሎት አገልግሎት ናቸው። 

 

  1. ጋብቻና ቤተሰብ፦

 

  • ጋብቻ በእግዚአብሔር የተመሠረተ ቅዱስ ተቋም ሲሆን፣ ጅማሬውም በኤደን ገነት በአዳምና ሔዋን ተጀምሯል። 
  • ክፍሉ ለቅድመ ጋብቻ ምክር፣ ለድህረ ጋብቻ ትምህርታዊ ክትትል፣ ለመሪዎች ቤተሰብ ጥንካሬና ለጥንድ አገልጋዮች የአሰልጣኞች ስልጠና (TOT) ትኩረት ይሰጣል። 
  • አገልጋዮችና መሪዎች በቅድሚያ የራሳቸውን ቤተሰብ በመልካም ምሳሌነትና በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያ መምራት እንዳለባቸው ያሳስባል። 

 

  1. የጸሎት አገልግሎት፦

 

  • ጸሎት ለቤተክርስቲያን ተሐድሶና ለሁለንተናዊ ዕድገት መሠረት ሲሆን በሦስት ዋና ዋና ደረጃዎች ይከናወናል፦ 

 

  • የግል ጸሎት፦ እያንዳንዱ አማኝ ከአምላኩ ጋር የሚገናኝበትን የግል የጸሎት ማዕከል መገንባት ይኖርበታል። 
  • የቤተሰብ ጸሎት፦ በቤተሰብ ደረጃ የጸሎት ማዕከል በመገንባት የትውልድ እርግማንን መስበርና ልጆችን በመንፈሳዊ መንገድ ማደግ ይገባል። 
  • የጉባኤ/የቤተክርስቲያን ጸሎት፦ እግዚአብሔርን ማወደስ፣ ንስሐ መግባት፣ ልመናና ምልጃ ማድረግ፣ እንዲሁም የክፉውን ሥራ የሚያፈርስ የተቃውሞ ጸሎት ማድረግን ያካትታል። 





ፎቶዎች

የመምሪያው አመራር

ስም

የመምሪያ ኃላፊ

የመምሪያው የመገናኛ መረጃ

ሞባይል: +251-9 12 34 56 78
ቢሮ: +251-9 12 34 56 78
ፋክስ: +251-9 12 34 56 78
ኢሜይል: @ekhc.et