ፋይናንስ መመሪያ

ስለ መምሪያው

 

….የመቅደሱ በረኞች ከሕዝቡ የሰበሰቡትን ወደ እግዚአብሔር ቤት የገባውን ገንዘብ ይደምር ዘንድ ወደ ካህናቱ አለቃ ወደ ኬልቂያስ ሂድ….. 2ኛ ነገ 22፡4

 

  • የመቅደሱ በረኞች ከህዝቡ የሰበሰቡትን ወደእግዚአብሄር ቤት የገባውን ገንዘብ ይደምር ዘንድ ወደ ካህናቱ አለቃ ኬልቂያስ ሂድ ሲለው እንመለከታለን።

እንግዲህ ንጉሱ ፀሀፊውን የሚያዘው ምን እንዲያደርጉ ነው 

  1. ከህዝቡ የተሰበሰበውን ወደ እግዚአብሄር ቤት የገባውን ገንዘብ ይደምሩ ዘንድ
  2. ለሰራተኞች ማለትም ለአናጢዎች ለድንጋይ ወቃሪዎች መቅደሱን ለሚጠግኑ እንዲከፍል እንዲሁም ለመቅደሱ ጥገና የሚውሉ የተመረጡ እንጨቶች እና የተቀረፁ ድንጋዮችንም ይገዙ ነበር።
  • ዕዝራ 1፡ 7-8 ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወስዶ በአማልክቱ ቤት ያኖራቸውን የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃዎች አወጣ የፋርስ ንጉስ ቂሮስም በመዝገቡ ላይ በነበረው በሚትረዳጡ እጅ አወጣቸው ለይሁዳም መስፍን ለሰሳብሳር ቆጠራቸው፡፡
  • የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ በመዝገቡ ላይ እንደነበረው አወጣ።
  • ቆጥሮ ለይሁዳው መስፍን አስረከበ።

ስለዚህ በብሉይ ኪዳንም የሂሳብ አያየየዝ ነበር ማለት ነው፡፡ ገቢ እና ወጪዎች በአግባቡ ተደምሮ እና ተሰንዶ መያዝ እንዳለበት ያሰየናል፡፡ 

ዛሬ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ዋናው ተልኮአችን          

 ማቲ 28፡ 19 -20
“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኃቸው ያዘዝኃችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኃቸው ደቀመዛሙርቴ አድርጋቸው፤ እነሆ እኔ እስከአለም ፍፃሜ ድረስ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፡፡”  

ይህን ተልዕኮ ከምንፈፀምበት መንገድ አንዱ ይህ ዛሬ የጀመርነው ፕሮጀክት አንዱ ነው፤ ወንጌልን ላልሰሙት በቋንቃቸው ማድረስ   የፋይናንስ ስራ በቤተክርስቲያን ውስጥ አገልግሎት ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ለሚካሄደው ሰዎችን በወንጌል የመድረስ ተልዕኮ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ነው።

ፋይናንስ ማለት የገንዘብ አስተዳደር ማለት ነው፡፡ ገቢዎችንና ወጪዎችን በመረጃ የተደገፈ መሆን ይኖርበታል፡፡

  • በኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት የሚንቀሳቀስ ገቢዎችን እና ወጪዎችን በሰነድ በማስደገፍ፣ የፋይናንስ አስተዳደር መመሪያ በመቅረፅ በአግባቡ በማስተዳደር ላይ ትገኛለች:: 
  • የቤተክርስቲያን ገቢ በአጥቢያ ደረጃ ከአባላቶች፤ ከአስራት፣ ከመባ እንዲሁም ከፍቅር ስጦታዎች ሊገኝ ይችላል። 
  • ህብረቶች እና ቀጠናዎች እንደየመዋቅራቸው ገቢዎችን በፐርሰንት ወይም በኮታ አስተዋፅኦ ከአጥቢያዎች ያገኛሉ።
  • ዋናው ፅ/ቤት ገቢዎችን ከቀጠናዎች እና ከህብረቶች የሚሰበስብበት አግባብ አለው፡፡ እንዲሁም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ከሚደግፉ አለም አቀፍ አጋር ረጂዎች ገቢን ያገኛል።
  • እያንዳንዱ ወጪ፤ በወጪ ሰነድ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡ ከዋና ጽ/ቤት ወደ ፕሮጀክቶች የሚላኩ ገንዘቦች በተላኩበት የበጀት ዓይነት በሰነድ መወራረድ አለበት።
  • ለምሳሌ 

የደመወዝ ወጪ በፔሮል 

የቢሮ ክራይ በውል እና በደረሰኝ 

ግዢና አገልግሎቶች በመመሪያ መሰረት በሰነድ…..

  • ከገንዘብ አወጣጥ በፊት ለሚወጣ ገንዘብ የሥራ ዕቅድ ግንዛቤ ውስጥ ቀዳሚ ሥፍራ ሊኖረው ይገባል፤ 
  • ከረጂ አጋሮች የተገኘ ገንዘብም ሆነ በቤተክርስቱያኒቱ የተገኙ ሀብቶችን ለታቀደለት ዓላማ ብቻ በእቅዱ ዝርዝር መሠረት ጥቅም ላይ እንዲውል ፋይናንስ መምሪያ ጥብቅ ክትትል ያደርጋል፤
  • የገንዘብን አወጣጥና አጠባባቅ ጥንቃቄ በተሟላው ሁኔታ መፈጸሙን በሚገባ ማረጋገጥ፤
  •  ወጪዎች በአንድ ግለሰብ ሳይሆን በቡድን በሆነው መልኩ መከናወን መቻሉን በማወቅ አንድ ግለስብ ገንዘብ ወጪን ሲጠይቅ ለጠየቀው ገንዘብ በጀት መኖሩን ፡ የጠየቀው ገንዘብ በኀላፊዎች መፅደቁን(መፈረሙን) በማረጋገጥ የክፍያ ሰነዶችን በማዘጋጀት እንከፍላለን ህጋዊ በሆኑ ደረሰኖች እናወራርዳለን፡፡ 
  • ማንኛውም ግዢ በደረሰኝ መሆን ይኖርበታል፡፡ ግዢው አስፈላጊ ሆኖ ግን በከተማው ደረሰኝ ያለው አቅራቢ ከጠፋ በቃለ ጉባኤ ተይዞ እና ውል ተፈራርሞ በውሉ መሰረት ክፍያ ይፈፀማል ከዚህ ውጪ ምንም ክፍያ አይፈፀምም፡፡ 
  • ግዥዎች ከተፈጸሙ በኃላ የዕቃ ገቢ ማድረጊያ ደረሰኝ ተቆርጦ መያያዙን  ማረጋገጥ፤
  •  በሥልጠና ወቅትም ሆነ በማንኛውም ሁኔታ ክፍያ በሚፈጸምበት ጊዜ የአቴንዳንስ   ፊርማ ከክፍያ ፊርማ ጋር የፊርመ ናሙና ተመሳሳይ መሆናቸውን በሚገባ ማረጋገጥ፤

በመጨረሻም

  • ስለዚህ እኛ እንደፋይናንስ እነዚህን በጀቶች በሚገባ ማስተዳደር ሪፖርት ማዘጋጀት እና ለሚመለከተው ሁሉ  በአግባቡ ታማኝ ግልፅ እና ጊዜው የጠበቀ ሪፖርት በማዘጋጃት በውጪ ኦዲተር ኦዲት በማስደረግ፤ ኦዲት የተደረገ የፋይናንስ ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤ እናቀርባለን፡፡

“….ለአገልግሎቱ ሾመኝ ታማኝ አድረጎ ስለቆጠረኝ….” 1ኛ ጢሞቶዎስ 1፡ 12

ፎቶዎች

የመምሪያው አመራር

ስም

የመምሪያ ኃላፊ

የመምሪያው የመገናኛ መረጃ

ሞባይል: +251-9 12 34 56 78
ቢሮ: +251-9 12 34 56 78
ፋክስ: +251-9 12 34 56 78
ኢሜይል: @ekhc.et