የሴቶች አገልግሎት ክፍል

ስለ መምሪያው

መግቢያ

ከመጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን (ኢ.ቃ.ሕ.ቤ) ውስጥ ያሉ ሴቶች ከባሎቻቸውና ከወንድሞቻቸው ጎን ለጎን በታማኝነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ሆኖም በ1990 እ.ኤ.አ. ብሔራዊ የሴቶች አገልግሎት እስከተቋቋመበት ጊዜ ድረስ ያደረጉት አስተዋጽኦ ብዙውን ጊዜ ዕውቅና አላገኘም ነበር። በ1992 እ.ኤ.አ. አገልግሎቱ ከአጥቢያ እስከ ብሔራዊ ደረጃ የተቀናጀ መዋቅር የዘረጋ ሲሆን፣ ይህም ሴቶች በመንፈሳዊ ሁኔታ እንዲያድጉ፣ የአመራር ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ፣ እንዲሁም በቤታቸው፣ በቤተ ክርስቲያናቸው እና በማኅበረሰባቸው ውስጥ ንቁ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ አስችሏቸዋል። 

በዓመታት ሂደትም መምሪያው የአገልግሎትና የሥልጠና ጽሕፈት ቤቶችን አደራጅቷል፤ የሴት መሪዎችን አቅም ገንብቷል፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ ሥልጣንና ቦታ እንዲያገኙ አድርጓል፤ የሙያና የአገልግሎት ሥልጠና ማዕከላትን አስጀምሯል፤ ለሴት አገልጋዮችና ለችግረኛ ተማሪዎች የትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) መስጠቱን ቀጥሏል፤ የወንጌላውያንን ልጆች ደግፏል፤ እንዲሁም ሴቶች በኅብረተሰቡና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ተዛማጅ የሥልጠና ቁሳቁሶችን አቅርቧል።

ተልዕኮ

 

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውን ታላቁን ተልዕኮ እንዲፈጽሙና ወንጌል ለሁሉም ተዳራሽ እንዲሆን ሴቶችን ለሁለንተናዊ ዕድገት ማስታጠቅና ማብቃት፣ በዚህም እግዚአብሔርን ማገልገል ነው።

ራዕይ

 

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ሴቶች ጠንካራ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ሆነው፣ የተቀየረ ክርስቲያናዊ ሕይወት ሲኖሩ፣ የክርስቶስ አምባሳደሮች ሆነው ሲያገለግሉ፣ እና እግዚአብሔር ባስቀመጣቸው ቦታ ሁሉ በአርአያነታቸው የተሐድሶ አገልጋዮች ሆነው ማየት ነው። 

 

ግብ

 

በኢትዮጵያና ከዚያም ባሻገር ያሉ ሴቶች ወንጌልን እንዲሰሙ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ፣ የክርስቶስ አምባሳደር እንዲሆኑ፣ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲለማመዱ፣ እና በቤተ ክርስቲያንና በሰፊው ማኅበረሰብ ውስጥ ቀና ተጽዕኖ እንዲያመጡ በማድረግ እግዚአብሔርን ማክበር ነው። 

 

ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች

 

1. ሴቶችን በተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ማስታጠቅና ማሳተፍ

 

  • ሴቶችን በታማኝነት እንዲያገለግሉ በመንፈሳዊ ጥንካሬ፣ በአመራር ክህሎትና በተግባራዊ መሳሪያዎች ማዘጋጀት። 
  • ለተከታዩ ትውልድ አቅም ለመገንባት ወጣት ሴቶችንና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ማማከርና መንፈሳዊ መካሪነት መስጠት። 
  • በመጽሐፍ ቅዱሳዊ የጋብቻ ምክር ቤተሰቦችን ማጠናከር። 
  • እናቶች ልጆቻቸውን በእምነት እንዲያሳድጉ ማስታጠቅ። 
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አማካኝነት ሴቶችን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ማነፅና ማጽናት። 
  • የጸሎትና የምልጃ ሕይወት ባህልን ማዳበር። 
  • የአገልጋዮች ሚስቶችን በደቀ መዝሙርነትና በምክር አገልግሎት መደገፍ። 
  • በወንጌል እውነተኝነት፣ በድፍረትና በርኅራኄ የምስራቹን ማሰራጨት። 
  • በሴቶች አገልግሎት ውስጥ ደቀ መዝሙርነትን ማስፋፋት። 

2. የሴቶችን አገልግሎት በጥንካሬ የአመራርና የክትትል መዋቅር ማደራጀት

 

  • የሴቶችን አገልግሎት ከአጥቢያ እስከ ብሔራዊ ደረጃ የሚያስተሳስሩ መዋቅሮችን መገንባት። 
  • ጠንካራና የታጠቁ ሴት መሪዎችን ማባዛት። 
  • የተደራጁ ጽሕፈት ቤቶች፣ ሀብቶችና የሰው ኃይል አቅም እንዲኖሩ መሞገትና ማመቻቸት። 
  • በሥራ ቦታዎች ለሙያተኛ ሴቶች እኩል ዕድሎችን ማሳደግ። 
  • የጾታ እኩልነት እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ እንዲሁም በፖሊሲዎችና ሕጎች ዝግጅት ላይ አስተዋጽኦ ማድረግ። 

3. ለሥነ–መልኮታዊና ተግባራዊ ተጽዕኖ ሥልጠናና ትምህርትን ማመቻቸት

 

  • ለኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳደጊያ የሚሆኑ የሙያ ሥልጠናዎችን መስጠት። 
  • የግንዛቤ ማስጨበጫና የመብት ተሟጋችነት ሥልጠናዎችን መስጠት። 
  • ሴቶች በቤት፣ በቤተ ክርስቲያን፣ በማኅበረሰብና በዓለም ላይ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ ማስታጠቅ። 
  • በሥነ–መልኮት፣ በማኔጅመንትና በሙያዊ ዘርፎች የትምህርት ዕድሎችን መፍጠር። 
  • ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን መቃወምና መሞገት። 

4. ሴቶችን በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሥራዎች ማብቃት

 

  • ሴቶችን በአነስተኛ ንግድ ሥራ ስልቶች ማሰልጠን። 
  • በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ ተግባራዊና መንፈሳዊ ፍላጎቶችን ምላሽ መስጠት። 
  • በወንጀለኞች/ማረሚያ ቤት አገልግሎት አማካኝነት ተስፋንና እድሳትን ማምጣት። 
  • የቲሞችንና ተጋላጭ ልጆችን በፍቅርና በፍላጎት አቅርቦት መደገፍ። 
  • የክርስቶስን ርኅራኄ አርአያ በማድረግ ሴቶችን ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማነሳሳ

ፎቶዎች

የመምሪያው አመራር

ስም

የመምሪያ ኃላፊ

የመምሪያው የመገናኛ መረጃ

ሞባይል: +251-9 12 34 56 78
ቢሮ: +251-9 12 34 56 78
ፋክስ: +251-9 12 34 56 78
ኢሜይል: @ekhc.et