የማኅበራዊ ዋስትና ኮሚሽን

ስለ መምሪያው

ታሪካዊ ዳራ 

የቤተክርስቲያኒቱ አመሰራረት ታሪክ የሚጀምረዉ በእግዚአብሄር አምላክ ጥሪና በመንፈስ ቅዱስ ምሪት መነሻቸዉን ባህር ማዶ ካደረጉ የኤስ አይ ኤም የወንጌል መልዕክተኞች በእንግድነት ምድር በመንከራተትና መስዋዕትነት በመክፈል ከ1920 ዓ.ም የካቲት ወር ጀምሮ ካመጡት  የምስራች ቃል ብስራት ጋር ተያይዞ ህዝቦችንን ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን  ካሸጋገረው  የወንጌል ስርጭት ታሪክ ሂደት ጋር ተያይዞ የቀጠለ ንቅናቄ ውጤት  ነዉ፡፡ 

በእነኘሁ ጥቂት የወንጌል መልዕክተኞች መሣሪያነት የተለኮሰዉ የምስራች ቃል ችቦ ጥቂት በነበሩ የየመንደሩ ወጣቶች አስደናቂ መሰጠትና ሁለንተናቸዉን ለበራላቸዉ የወንጌል አገልግሎት በማዋላቸዉ በአጭር ጊዜ የምስራች ቃሉ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሎ የባዕድ አምልኮ ጨለማን በመግፈፍ በየማሕበረሰቡ  አስደናቂ መንፈሳዊና ማሕበራዊ ለዉጦች እየተመዘገቡ በንጽጽር ሲታይ አሁን ላለንበት  ከአዕምሮ በላይ ለሆነ  እድገትና እምርታ መድረሳችን በእጅጉ ያስደንቃል፤ ያስገርማል፡፡ 

ከላይ በአጭሩ በተገለጸዉ የአምላካችን አስደናቂ ዕቅድና ክንዉን እንዲሁም በጥቅት ሚስዮናዊያን ፈር ቀዳጅነትና   በቀደምት አባቶች ያላሰለስ ተጋድሎና መስዋዕትነት  የተነሳ ዛሬ የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን  በመላ የሀገራችን ክፍሎችና በአለም አቀፍ መድረኮች ከጠባቂዋና ከመሪዋ የተሰጣትን፣ መንግስቱን በምድር የማስፋፋትና ነፍሳትን ወደ ዘላለም ህይወት የመማረክ ተልዕኮዋን በመፈጸም ላይ ትገኛለች፡፡

ቤተክርሲቲያኒቱ በምድር ላይ የመኖሩዋ  ዋና ዓላማ የሆነዉን ነፍሳትን ወደ ድነት ማምጣትና የእግዚአብሔርን መንግስት የማስፋት ሥራዋን ለመፈጸም ከዋና ጽ/ቤት ጀምሮ እስከ አጥቢያዎች ድረስ በተደራጁ መዋቅሮች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አገልጋዮችና ሰራተኞችን አሰማርታ ሁለንተናዊ አገልግሎት ትሰጣለች፡፡

በቤተክርሲቲያኒቱዋ የተለያዩ መዋቅሮች የተሰማሩ አገልጋዮችና ሠራተኞች የአገልግሎት ዘመናቸዉን ፈጽመዉ በጡረታ ሲገለሉ የሚደርስባቸዉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተገዳሮቶች ለመkkምና ለማስወገድ ታስቦ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የማኀበራዊ ዋስትና ኮሚሽን በመጋቢት 22 ቀን 1999 ዓ.ም በሲዳማ ያናሴ አፈራራ በተካሄደዉ 46ኛው ጠቅላላ ጉባዔ የተመሰረተ ሲሆን፣ የቤተክርሲቲያኒቱ አገልጋዮችና ሠራተኞች በጡረታ ዋስትና ደንብ እንዲተዳደሩ በተወሰነው መሰረት የጡረታ መመሪያ ደንቡን ከተመሳሳይ እህት ቤ/ክ እና ከመንግስት ማህበራዊ ዋስትና የጡረታ አዋጅ ተወስዶ በአውዱ መሰረት መሻሻል ያለበት አንቀጾችን በማስገባትና በማሻሻል ብቁነቱ በሕግ ባለሙዎች ተረጋግጦ ከየካቲት 1 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ በዋና ጽ/ቤት በማስተባበሪያ ደረጃ ቢkkምም ቤተክርስቲያናችን ከደረሰችበት የመንፈሳዊና የማህበራዊ የልማት እድገት ሥራዎች አገልግሎት እየሰፋ በመምጣቱ የአገልጋዩ እና የሠራተኛው ቁጥር እየጨመረ ስለመጣ በዋና ጽ/ቤት ዋና ቢሮ በመክፈትና በሁለት ትልልቅ ቀጠናዎች የቅርንጫፍ ቢሮዎችን በመክፈት ቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ጠባቂነት በቦርድና በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በመመራት በቁጥር በርከት ያሉ አባላትን በማኀበራዊ ዋስትና ፈንድ ውስጥ በማካተት ከ100 በላይ የሆኑ አባቶችንና እናቶችን የማህበራዊ ዋስትና  አበል ተጠቃሚ በማድረግ እየሠራ ይገኛል ፡፡ 

አብይ ተግባራት 

  • የጡረታ መዋጮ መሰብሰብ፣ የጡረታ አበል ክፍያ መፈጸምና የጡረታ ፈንዶችን ማስተዳደር
  • የጡረታ ፈንዶችን ከወጪ ቀሪ በኢንቨስትመንት ላይ በማዋል ገቢውን ማዳበር
  • በጡረታ ዕቅድ ለተሸፈኑ የቃ/ሕ/ቤ/ክ ሰራተኞችና አገልጋዮችን መከፈሉን ማረጋገጥ 
  • የኢ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ/ማ/ዋ/ኮ ፕሮግራሞች እንዲጠናከሩና እንዲስፋፉ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣  
  • ምዝገባ ማካሔድና ማስረጃዎችን ማደራጀት፣

ራዕይ     

በቤተክርሲቲያኒቱ መዋቅር ዉስጥ ያሉ ሁሉም አገልጋዮችና ሠራተኞች በዕድሜም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ከአገልግሎትም ይሁን ከሥራ ስሰናበቱ የዘለቄታ ማኀበራዊ ዋስትና ተጠቃሚ በመሆን ከሚደርስባቸዉ እኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀዉስ ተላቀው ማየት፣  

ተልዕኮ

  • የጡረታ አቅድ የተሸፈኑ አባላት ገቢ በዕድሜ፣በጤና ጉድለት፣በሥራ ላይ ጉዳትና በሞት ምክንያት ሲkረጥ በተቀላጠፈ መንገድ አገልግሎት በመስጠት በመመሪያው መሰረት በገቢ መደገፍ፣
  • የኢ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ/ማ/ዋ/ኮ ፈንድን ማጠናከርና አቅምን  ማሳደግ፣ 
  • የኮሚሽኑን ሽፋንና ፕሮግርም ማስፋት፣ የአገልጋዮችና የሠራተኞች የማህበራዊ ሥርዓቶች እንዲጠናከሩ ማድረግ፣       
  • በየደረጃዎቹ በሚገኙ መዋቅሮች ዉስጥ የተሰማሩ አገልጋዮችና ሠራተኞች በማኅበራዊ ዋስትና አገልግሎት እንዲታቀፉ ማድረግ  
  • ከአገልጋዮችና ሠራተኞች  እንዲሁም ከአሰሪዎች የሚሰበሰብ ገንዘብ ለታለመለት አገልግሎት ብቻ መዋሉን በማረጋገጥ ማስተዳደር 
  • በዋስትናዉ የታቀፉ አገልጋዮችና ሰራተኞች በስንብት ወቅት ያለ ዉጣ ዉረድ ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡  

እሴቶች

  • በእግዚአብሔር ቃል መደገፍ
  • መንፈሳዊ አንድነት
  • የወንጌል ባለአደራነት
  • ቅንጂታዊ አሰራር
  • እርስ በርስ መረዳዳት 
  • ታማኝነት 
  • ግልጽኝነት
  • ሐላፊነትና ተጠያቂነት
  • ቅድስና እና ጸሎት

ፎቶዎች

የመምሪያው አመራር

ስም

የመምሪያ ኃላፊ

የመምሪያው የመገናኛ መረጃ

ሞባይል: +251-9 12 34 56 78
ቢሮ: +251-9 12 34 56 78
ፋክስ: +251-9 12 34 56 78
ኢሜይል: @ekhc.et