1) 15ቱን ቀጣናዎችና 10 ልዩ የአጥቢያ ቤ/ክ ሕብረቶች መሪዎችን መተዋወቅ፥ ጉብኝት ማድረግና የአገልግሎታችንን/የሥልጠና ክፍላችንን ራዕይ ማስጨበጥ፤ በቤ/ክ ወቅታዊ ችግሮችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ዙሪያ ዉይይት በማድረግ መረጃዎችን መሰብሰብ
2) ቃለ ሕይወ ትን በአቋማ ወጥና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማድረግ/በአንድ ገጽ ለማስቀመጥ፥ የእምነት አቋሟን፥ መተዳደሪያ ደንቧንና ሌሎች ተያያዥ ደንቦችንና ሥርዓቶችን በጥልቀት መርምሮ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ለወቅቱ የሚያገለግል ሰነድ እንዲዘጋጅ የማስተባበር አገልግሎት መስጠት
3) የቤ/ክንን የመድረክ አገልግሎት በተለይም የስብከት አገልግሎትን መጽሐፍ ቅዱስን ገላጭ (ገላጭ ስብከት) እንዲሆን ሥልጠና በማመቻቸት ለሰባኪዎች መስጠት
4) ሐሰተኛ ኒቢያትና ሐዋርያትን በተመለከተ ቤ/ክኒቱ ወጥና ግልጽ አቋም እንዲኖራት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ማዘጋጀትና በተዋረድ ሥልጠና በመስጠት ቃለ ሕይወትን ወደ አንድ ገጽ ማምጣት
5) የእረኝነት አገልግሎት ሥልጠና በመስጠት (በመጋቢያንና በሽማግሌዎች አመራር ዙሪያ የሚታየዉን ግራ መጋባት ወጥና መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዲሆን ወጥ የሆነ የአመራር አካል በቃለ ሕይወት ሁሉ እንዲኖር ማመቻቸት
6) ሳናዉቅ የተቀላቀለንን አጉል ባሕልንና ባሕላዊ አምልኮን ከቤ/ክ ለማዉጣት ዛሬ ላይ ወደ ዉስጥ ዘልቀዉ የገቡ ልዩ ልዩ ባሕላዊ ብቻ ሳይሆኑ አምልኮአዊ ልምምዶችን በመጽሐፍ ቅዱስ እና በቤ/ክ ታሪካዊ ዐዉድ በመፈተሽ አስፈላጊዉን እርምት እና ማስተካከያ ሥልጠና በጥንቃቄ አዘጋጅቶ በዐዉደ ጥናት መልክ በመስጠት ቤ/ክንን ካንዣበበባት አደገኛ የአምልኮ ዝቅጠት መታደግ
7) አጥቢያ ተኮር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልማት (የዳኮኒያ አገልግሎት) የሚጀመርበትንና የሚጠናከርበትንና ልማትን በሚመለከት የአመለካከት ለዉጥ የሚያመጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን በመስጠት ሕዝባችንን ከድፐንዳንሲ ሲንድሮም በሥራ ወደ መትጋት በመመለስ አጥቢያ ቤ/ክንን የለዉጥና የመልካም ተግባር ማዕከል ማድረግ
የNMLTM አገልግሎት የትኩረት አቅጣጫዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ማሳያ ትምህርት
የሐዋ ሥ. 20፥17-38
በዚህ ትምህርት ሐዋርያዉ ጳዉሎስ የቤ/ክ መሪነትን በተገቢ ሆኔታ እንዲወጡ ለኤፌሶን ቤ/ክ የጣቸዉን አምስት ታላላቅ ምክሮች ይካተታሉ
እነርሱም፦
የመጀመሪያዉ
ሁለተኛዉ
የሥልጠና ትምህርት እርሻን እንደ እግዚአብሔር (Farming God’s way) በሚል የመሬትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አያያዝንና ምርታማነትን የመጨመር አዲስ ትምህረት ተሰጥቶአል። ይህ በዋናነት መሬት በጥልቀት ሳይታረስ እና ሳይረበሽ የተሻለ ምርት የማምረትና በእርሻ ምክንያት አፈሩን ከመታጠብ ለመታደግ የሚያስችል በቅርብ ጊዜ ተጀመረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ አስተራረስንና አመራረትን የሚያስተምር ሥልጠና ነዉ።
በዚህ ረገድ በ8 ቀጣናዎችና በሦስት ልዩ ሕብረቶች በርካታ መሪዎችን ማለትም የአባቶች፥ የሴቶች፥ የወጣቶችን፥ መጋቢያንንና ወንጌላዊያንን ጨምሮማሰልጠን ተችሎአል።
እስካሁን ሥልጠናዉ የተካሃደባቸዉ ሥፍራዎች ፦
ሲሆኑ ሥልጠናዉ የሚያስፈልጋቸዉ 7 ቀጣናዎችና 7 ልዩ ሕብረቶች በድምሩ 14 ገና ይቀራሉ። እነዚህን ቀጣናዎች ለማገልገል የተጓዝነዉ ርቀት 13,243 ኪሎ ሜትር ነዉ።

የመምሪያ ኃላፊ
ሞባይል: +251-9 12 34 56 78
ቢሮ: +251-9 12 34 56 78
ፋክስ: +251-9 12 34 56 78
ኢሜይል: @ekhc.et