የሙያተኞችና የንግድ ዘርፍ ደቀ መዝሙርነት አገልግሎት

ስለ መምሪያው

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በ1927 እ.ኤ.አ. በአሜሪካዊው ሚሲዮናዊ በዶክተር ቶማስ ላምቢ የተመሠረተች፣ ከ12 ሚሊዮን በላይ ምዕመናንና ከ14,000 በላይ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ያሏት በሀገሪቱ ትልቋ ቤተ ክርስቲያን ናት። ላለፉት 98 ዓመታት በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ መንፈሳዊና ልማታዊ አገልግሎቶችን ስትሰጥ ቆይታለች። 

የኢ.ቃ.ሕ.ቤ የሙያተኞችና የንግድ ዘርፍ ደቀ መዝሙርነት አገልግሎት (Professionals Ministry / Discipleship Marketplace Leadership – DML) ምዕመናን የተፈጠሩት በዓላማና ለዓላማ መሆኑን በማሳሰብ፣ በሁሉም የሕይወት ዘርፎችና የሥራ ቦታዎች ክርስቶስን የሚያከብር አምልኮታዊ ሕይወት እንዲኖሩ ያነሳሳል። 

 

ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዋና ዋና ዓላማዎች

  • ራዕይ፦ በቤተ ክርስቲያን ላይ የተመሠረተ የንግድ አገልግሎትን (Business as Mission) በመጠቀም የንግድና የሥራ ቦታውን (Marketplace) መዋጀት እና በክርስቶስ ጌታነት ስር ማድረግ። 
  • ተልዕኮ፦ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ስኬታማ የሥራ ቦታ አገልጋዮችን እንዲያፈሩ ማብቃት፣ እንዲሁም የንግድ ባለቤቶች በአራት አቅጣጫዎች (በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚ እና በአካባቢ ጥበቃ) ውጤታማ እንዲሆኑ ማሰልጠን፣ ማበቃትና ደቀ መዝሙር ማድረግ። 

 

የአገልግሎቱ 3 ዋና ዋና አምዶች (Pillars)፦

  • ማስታጠቅ (Equipping)፦ እያንዳንዱ አማኝ የድኅነትን ወንጌል መልእክት ወደ ሥራ ቦታው ይዞ እንዲሄድ ማስታጠቅ። 
  • ደቀ መዝሙር ማድረግ (Discipling)፦ አማኞች ሥራቸውን እንደ አምልኮ አድርገው እንዲኖሩ ደቀ መዝሙር ማድረግ። 
  • ማብቃት (Empowerment)፦ ባለሀብቶችና የንግድ ሰዎች በንግዳቸው አማካኝነት እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ ማብቃት። 

የአገልግሎቱ አጭር ታሪክ

አገልግሎቱ የተጀመረው በ2016 እ.ኤ.አ. በኢቫንጀሊካል ቲኦሎጂካል ኮሌጅ (ETC) በተዘጋጀ የመጀመሪያው የDML ወርክሾፕ አማካኝነት ነው። ወርክሾፑን በዋና አሰልጣኝነት የመሩት ዶ/ር ሬኒታ ሪድ ቶምሰን እና ዶ/ር ፊል ዎከር ነበሩ። በስልጠናው ከተሳተፉት መካከል ፓስተር ዮሴፍ በቀለ የነበረውን ራዕይ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ጸሐፊ ለዶ/ር ኩርሴ ሼፈኖ እና ለምክትል ዋና ጸሐፊው ለዶ/ር ወይታ ወዛ በማካፈሉ፣ አገልግሎቱ በይፋ በኢ.ቃ.ሕ.ቤ ዋና መሥሪያ ቤት ስር ተቋቋመ። 

በመቀጠል ከKingdom Priest Ministries (KPM) ጋር በመተባበር 96 የንግድ ሰዎችን ማሰልጠን ተጀመረ። በኬንያ ከተሰጠ የአሰልጣኞች ሥልጠና (TOT) በኋላ ማኑዋሎችና አቅጣጫዎች ተዘጋጅተው አገልግሎቱ በ2017 እ.ኤ.አ. መደበኛ ጉዞውን ጀመረ። 

 

ከማን ጋር እንሠራለን?

የሙያተኞችና የንግድ ዘርፍ አገልግሎት ከሚከተሉት ክፍሎች ጋር በትብብር ይሰራል፦

  • በሁሉም የኢ.ቃ.ሕ.ቤ መዋቅሮችና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት 
  • የንግድ መሪዎች ህብረቶችና የንግድ ቡድኖች 
  • ወጣቶችና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች 
  • የቤተሰብ፣ የሴቶችና የሕፃናት አገልግሎቶች 
  • የሥነ–መልኮት ትምህርት ቤቶችና የባይብል ኮሌጆች 
  • የማረሚያ ቤት አገልግሎት፣ አርሶ አደሮች እና ሚሲዮናዊ ላኪ ድርጅቶች 

 

ቁልፍ ፕሮግራሞችና የተመዘገቡ ውጤቶች

  • ሥልጠናዎች፦ የንግድ ሥራ ለወንጌል ተልዕኮ (Business as Mission)፣ መሠረታዊ የንግድና የቆጠባ ክህሎት፣ የሥራ ሥነ–ምግባር፣ ሥራ ፈጠራ፣ የጊዜና ንግድ ማኔጅመንት፣ አመራርነት፣ ታማኝነትና የመጋቢነት ሕይወት። 
  • ምክርና ድጋፍ፦ ለግለሰቦችና ለንግድ ተቋማት የክትትልና የሜንቶርሺፕ አገልግሎት መስጠት። 
  • ተጽዕኖዎች፦
    • የሙያተኞችና ባለሀብቶች የግልና የቤተሰብ ጽሞና ሕይወት ማደግ። 
    • በሥራ ቦታዎች ላይ ጨውና ብርሃን በመሆን ታማኝ ግብር ከፋይ መሆንና ከመንግሥት ዕውቅና ማግኘት። 
    • የቤተ ክርስቲያን ገቢና የአስራት/በኩራት መጠን መጨመር። 
    • የሥራ አጥነት ቁጥር መቀነስና አካባቢን የሚጠብቁ የኢንቨስትመንት ሥራዎች መስፋፋት። 
    • በታራሚዎች ዘንድ ንግድ ተጀምሮ ወደ ያልተደራሱ አካባቢዎች ሚሲዮናውያንን መላክ መቻሉ። 
    • የወንጌላውያንና ሚሲዮናውያን ሚስቶች በገቢ ማስገኚያ ሥራዎች እንዲበቁ ብድርና ድጋፍ ማመቻቸት። 

ፎቶዎች

የመምሪያው አመራር

ስም

የመምሪያ ኃላፊ

የመምሪያው የመገናኛ መረጃ

ሞባይል: +251-9 12 34 56 78
ቢሮ: +251-9 12 34 56 78
ፋክስ: +251-9 12 34 56 78
ኢሜይል: @ekhc.et